=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
እስቲ አንዴ ወደ ቀኝህና ወደ ግራህ ዘወርብለህ ተመልከት። በችግር የተፈተነ ወይም በጉዳት የሚሰቃይ እንጂ ሌላ ይታይሃልን? በየጓዳው የሚያለቅስ ፤ በየጉንጩም ላይ እንባ አይጠፋም።
ብዙ ተጐጅዎችና ብዙ ታጋሾችም አሉ። አንተ ብቻ አይደለህም የምትሰቃየው እንዲያውም ከሌሎቹ አንፃር ያንተ ስቃይ እጅግ የቀለለ ነው። ስንት ከአልጋው ላይ ተጋድሞ ለዓመታት ሳይነሳ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተገላበጠ ከህመሙ የሚሰቃይ ፣ በቁስሉ የሚጮህ አለ። ስንትስ እስረኛ አለ በዓይኑ ፀሀይን ሳያይ እስርቤት ውስጥ ብዙ ዓመታትን ያስቆጠረ? ስንቶቹስ ወንዶችና ሴቶች አሉ የአብራካቸውን ክፋዩች በጋለ እድሜያቸው ያጧቸው?
ስንትና ስንት ችግረኛ ፣ ብድር ያለበት ፣ ጉዳተኛ እና ከስቃይ የሚማቅቅም አለ። በነዚህ የምትፅናናበትና ይህች ህይወት የአማኞች እስርቤት እና የችግሮችና የጉዳቶች መንደር መሆኗንም የምታውቅበት ጊዜው አሁን ነው። ቤተመንግስታት በነዋሪዎቻቸው ደምቀው እንዳላነጉ ባዶዋቸውን ያመሻሉ። ቤተሰቡ ተሟልቷል ፣ የአካልም ጤንነት ይጠበቃል ፣ ሀብትም ተትረፍርፏል ፣ ልጆችም በዝተዋል ሲባል በጥቂት ቀናት ውስጥ ድህነት ፣ ሞት ፣ መለያያትና በሽታዎች ተጠራርተው ይመጣሉ።
--<({አል-ቁርአን 14:45})>--
«በነሱም እንዴት እንደሰራንባቸው ለናንተ ተገለፀላቹ ፤ ለናንተም ምሳሌዎችን ገለፅንላችሁ።»
ስለዚህ ጠንክር ብለህ ችግሮችን ማለፍ ይጠበቅበሃል። የደረሰብህንም ጉዳት በዙሪያህ ካሉትና ካንተ በፊት ኖረው ካለፉት ሰዎች ጉዳት ጋር ማነፃፀርም ይኖርብሃል። ያኔ ከነዚህ ሰዎች አንፃር ጤነኛ መሄንህን ትረዳለህ። ቀላል ጉዳቶችን እንጂ እንዳልተጎዳህም ትገነዘባለህ።
ስለዚህ ስለዋለልህ ውለታ አሏህን አመስግነው። ጉዳት እንዳያደርስብህ ስላስቀረልህም ነገር ሁሉ አወድሰው። የወሰደብህን ነገር በተሻለ እንዲተካልህም ከጅለው። በዙሪያህ ባሉትም ተፅናና።
በዚህም ታላቁ አርአያህ መልእክተኛው ሰ.ዐ.ወ ናቸው። በራሳቸው ላይ የእንግዴ ልጅ ተደርጎባቸው ፤ እግሮቻቸው እስኪደሙ ተመተው ፤ ፊታቸውን ተፈንክተው ፤ የዛፍ ቅጠል እስኪበሉ ድረስ ሸለቆ ውስጥ ታግደው ፤ ከመካ ተባረው ፤ የፊት ጥርሶቻቸው ተሰብረው ፤ የተከበረችውን ባለቤታቸውን (ዓኢሻ) ክብር አጉድፈውባቸው ፤ ሰባ ያህል ጓደኞቻቸው ተገድለው ፤ እሳቸው በህይወት ሳሉ ወንድ ልጃቸውና አብዛኛዎቹ ሴት ልጆቻቸው ሞተውባቸው ፤ ከረሃብ የተነሳ የሚበሉትን አጥተው ሆዳቸውን በድንጋይ አስረው ገጣሚ ፣ ድግምተኛ ፣ ጠንቇይ ፣ እብድና ውሸታም ተብለው አልፈዋል። ይህም ታላቅ መከራና አምሳያ የሌለው ፈተና ነበር። ከሳቸውም በፊት ዘከሪያ ተገድሏል ፤ የሕያም ታርዷል ፤ ሙሳም ታግዷል ፤ ኢብራሂምም (የአሏህ ወዳጅ) እሳት ላይ ተጥለዋል። ሁሉም ታላላቅ ሰዎች በተመሳሳይ ጐዳና ላይ አልፈዋል። ዑመር (ረ.ዐ) በደማቸው ተጥለቅልቀዋል ፤ ኡስማን (ረ.ዐ) ተገድለዋል ፤ ዐሊይ ተወግተዋል ፤ የኢስላም ምሁራን ጀርባዎቻቸውን ተገርፈዋል ፤ አማኞች ታስረዋል ፤ የአሏህ ደጋግ ባሮችም ተሰቃይተዋል።
--<({አል-ቁርአን 2:214})>--
«በእውነቱ የነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት ምዕመናን መከራ ቢጤ ሳይመጣባችሁ ገነትን ልትገነቡ ታስባላችሁ? መልክተኛውና እነዚያ ከሱ ጋር ያመኑት የአሏህ እርዳታ መቼ ነው? እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው ተርበደበዱም።»
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
|
---|